የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 27, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 1 እስከ ታኅሣሥ 27, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. በ1 ዜና መዋዕል 16:34 ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘው ሌዋውያን ዘማሪዎች ካዜሙት ስንኝ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? [w02 1/15 ገጽ 11 አን. 6, 7]
2. በ1 ዜና መዋዕል 24:7-18 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ዘገባ ከሉቃስ 1:5, 8, 9 ጋር ስናወዳድረው ስለ እውነተኛው አምልኮ ምን ያስተምረናል? [w05 10/1 ገጽ 11 አን. 8]
3. ንጉሥ ዳዊት፣ ልጁ ሰለሞን ስለ አምላክ ምን ዓይነት ስሜት እንዲያድርበት ፈልጎ ነበር? (1 ዜና 28:9) [w08 10/15 ገጽ 7 አን. 18]
4. የበርሜሉን መቀመጫ ለመገንባት የኮርማዎችን ቅርጽ መጠቀም ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው? (2 ዜና 4:2-4) [w05 12/1 ገጽ 19 አን. 3፤ w98 6/15 ገጽ 16 አን. 17]
5. በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ የነበሩት ሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች ብቻ ናቸው ወይስ ሌሎች ነገሮችም ነበሩ? (2 ዜና 5:10) [w06 1/15 ገጽ 31]
6. ከ2 ዜና መዋዕል 6:19, 22, 32 ምን እንማራለን? [w05 12/1 ገጽ 19 አን. 9፤ w06 11/1 ገጽ 18 አን. 4]
7. በ2 ዜና መዋዕል 13:5 ላይ “በጨው ኪዳን” የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? [w05 12/1 ገጽ 20 አን. 2፤ it-2-E ገጽ 842 አን. 7]
8. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 17:9, 10 ላይ ያለው ሐሳብ ለአገልግሎታችን እንደ መሠረታዊ ሥርዓት ልንመለከተው የምንችለው እንዴት ነው? [w09 6/15 ገጽ 12 አን. 7]
9. በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የአምላክ ሕዝቦች ከ2 ዜና መዋዕል 20:17 ጋር በሚስማማ መንገድ ምን ያደርጋሉ? [w03 6/1 ገጽ 21, 22 ከአን. 14-17]
10. ከንጉሥ ዖዝያን የዕብሪት ድርጊት ምን ትምህርት እናገኛለን? (2 ዜና 26:15-21) [w99 12/1 ገጽ 26 አን. 1, 2]