የወሩ ጭብጥ፦ “ቃሉን ስበክ፣ . . . በጥድፊያ ስሜት አገልግል።”—2 ጢሞ. 4:2
የመንግሥቱን መልእክት ለማዳረስ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀሙ!
1. ዳዊት ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?
1 ንጉሥ ዳዊት፣ ያጋጠመው ሁኔታ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ አላደረገውም። ለምሳሌ ዳዊት ለይሖዋ ቤት መሥራት ፈልጎ ነበር። ይህን ማድረግ እንደማይችል ሲነገረው ግን በግቡ ላይ ማስተካከያ በማድረግ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማዘጋጀት ጀመረ። (1 ነገ. 8:17-19፤ 1 ዜና 29:3-9) ዳዊት ማድረግ የማይችላቸውን ነገሮች እያሰበ ከመቆዘም ይልቅ ማድረግ በሚችላቸው ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጓል። እኛስ የመንግሥቱን መልእክት ለማዳረስ የሚያስችለንን አጋጣሚ በምንፈልግበት ጊዜ የዳዊትን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
2. ያለንበትን ሁኔታ ለማወቅ ምን ማድረግ እንችላለን?
2 ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ፦ ብዙዎች ረዳት ወይም የዘወትር አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሲሉ ኑሯቸውን ቀላል አድርገዋል። (ማቴ. 6:22) እናንተስ እንዲህ ማድረግ ትችሉ ይሆን? ያላችሁበትን ሁኔታ በጸሎት በምትመረምሩበት ጊዜ “ትልቅ የሥራ በር” እንደተከፈተላችሁ ታስተውሉ ይሆናል። ከሆነ አጋጣሚውን ከመጠቀም ወደኋላ አትበሉ።—1 ቆሮ. 16:8, 9
3. ሁኔታችሁ አቅኚ እንድትሆኑ ባይፈቅድላችሁ እንኳ ለመመሥከር የሚያስችሏችሁን የትኞቹን አጋጣሚዎች ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ?
3 ይሁንና ያላችሁበት ሁኔታ አቅኚ እንድትሆኑ የማይፈቅድላችሁ ቢሆንስ? እጃችሁን አጣጥፋችሁ ከመቀመጥ ይልቅ ሌሎች አጋጣሚዎችን ፈልጉ። ለምሳሌ ያህል፣ የሥራችሁ ባሕርይ ከማያምኑ ሰዎች ጋር የሚያገናኛችሁ ከሆነ ይህን አጋጣሚ ለምን ለመመሥከር አትጠቀሙበትም? ወይም ደግሞ የጤና ችግር ካለባችሁ የሕክምና ክትትል ለሚያደርጉላችሁ ሰዎች ለመመሥከር አጋጣሚውን ልትጠቀሙበት ትችሉ ይሆን? በዕድሜ ወይም ከባድ በሆነ የጤና ችግር ምክንያት የአቅም ገደብ ያለባቸው አስፋፊዎች 15 ደቂቃ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉበት ዝግጅት እንዳለ አስታውሱ። የወሩን ሪፖርታችሁን ስትመልሱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ያገለገላችሁትን ጊዜም መመዝገባችሁን አትርሱ፤ በተጨማሪም ትራክቶችን፣ የመታሰቢያ በዓል መጋበዣዎችንና የክልል ስብሰባ መጋበዣዎችን ጨምሮ ያበረከታችሁትን ጽሑፍ በሙሉ ሪፖርት አድርጉ። በእነዚህ አጋጣሚዎች ምሥክርነቱን በመስጠት የምታሳልፉት ጊዜ አነስተኛ ቢመስልም አንድ ላይ ሲደመር ምን ያህል ብዙ እንደሚሆን ስትመለከቱ ትገረሙ ይሆናል!
4. ምን ለማድረግ ቆርጣችኋል?
4 ሁላችንም ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ያገኘነውን አጋጣሚ ሁሉ ምሥራቹን ለማወጅ እንጠቀምበት። እንዲህ ስናደርግ ለመንግሥቱ ስንል ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንደሆነ ስለምናውቅ እርካታ ይሰማናል።—ማር. 14:8፤ ሉቃስ 21:2-4