ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 4-5
ከኢየሱስ የተራራ ስብከት የምናገኘው ትምህርት
ለመንፈሳዊ ፍላጎታችሁ ንቁዎች ናችሁ?
“መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ” የሚለው አገላለጽ ቃል በቃል “መንፈስ ለማግኘት የሚለምኑ” የሚል ትርጉም አለው። (ማቴ 5:3፤ ግርጌ) አምላክ የሚሰጠንን መንፈሳዊ እርዳታ የመቀበል ጉጉት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ
ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች በመዘጋጀትና በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት
ጽሑፎቻችንን እንዲሁም ጊዜ በፈቀደልን መጠን ድረ ገጻችን ላይ የሚወጡትን ትምህርቶች በማንበብ
JW ብሮድካስቲንግ ላይ በየወሩ የሚወጡትን ፕሮግራሞች ተከታትሎ በማየት
መንፈሳዊ ምግብ የመመገብ ልማዴን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?