የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sp ገጽ 11-12
  • አጋንንት ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አጋንንት ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!
  • የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ከአጋንንት የበለጠ ኃይል አለው
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • የክፋት ጠንሳሾች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • መላእክትንና አጋንንትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አጋንንት በእርግጥ አሉ?
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
sp ገጽ 11-12

አጋንንት ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!

ሰይጣንና አጋንንቱ ምንጊዜም ጨካኞችና አደገኞች ናቸው። በቀድሞ ዘመን ሰይጣን የታማኙን የኢዮብን ባሪያዎችና ከብቶች ገድሎበታል። ከዚያም “ኃይለኛ ነፋስ” አስነስቶ የነበሩበትን ቤት እንዲወድቅ በማድረግ አሥሩን ልጆቹን ገድሎበታል። ከዚያም በመቀጠል ኢዮብን “ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ ክፉኛ በሚያሠቃይ እባጭ” መቶታል።—ኢዮብ 1:7-19፤ 2:7

በኢየሱስም ዘመን አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን ዱዳዎችና ዓይነ ስውራን አድርገዋቸው ነበር። (ማቴዎስ 9:32, 33፤ 12:22) አንድን ሰው ራሱን በድንጋይ እንዲተለትል በማድረግ አሠቃይተውት ነበር። (ማርቆስ 5:5) አንድን ልጅም እንዲጮህ፣ መሬት ላይ እንዲወድቅና በኃይል ‘እንዲንፈራገጥ’ አድርገዋል።—ሉቃስ 9:42

ሰይጣንና አጋንንቱ፣ ኢዮብ ክፉኛ በሚያሠቃይ እባጭ እንዲታመም አድርገውት ነበር፤ አንድን ሰው ደግሞ ራሱን ስቶ እንዲወድቅና እንዲንፈራገጥ አድርገውታል

በቀድሞ ዘመን አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን እንዲታመሙ ሌሎችን ደግሞ ራሳቸውን ስተው እንዲወድቁና እንዲንፈራገጡ ያደርጓቸው ነበር

በዛሬው ጊዜ ሰይጣንና አጋንንቱ ከምንጊዜውም የበለጠ ነፍስ ለማጥፋት ታጥቀዋል። እንዲያውም ከሰማይ ተወርውረው ከተጣሉበት ጊዜ ወዲህ ክፉ ተግባራቸው ጨምሯል። ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ዘገባዎች የሰይጣንና የአጋንንቱን ጭካኔ ይመሠክራሉ። አንዳንዶቹን ሰዎች በበሽታ ያሠቃዩአቸዋል። ሌሎችን ደግሞ እንቅልፍ በመንሳት ወይም አስፈሪ ሕልም እንዲያልሙ በማድረግ በሌሊት ያሸብሯቸዋል። ሌሎችን ደግሞ በፆታ ያስነውሯቸዋል። ሌሎችን ደግሞ ያሳብዷቸዋል፣ ሰዎችን ወይም ራሳቸውን እንዲገድሉ ይገፋፏቸዋል።

አጋንንት አንድን ሰው ዓመፀኛ እንዲሆን ሲያደርጉት፤ ሌላን ሰው ደግሞ አስፈሪ ሕልም እንዲያልም በማድረግ ሲያስጨንቁት

በዛሬው ጊዜ አጋንንት አንዳንድ ሰዎችን ወንጀለኞች ያደርጓቸዋል፤ ሌሎችን ደግሞ በሌሊት አስፈሪ ሕልም እንዲያልሙ በማድረግ ያስጨንቋቸዋል

በሱሪናም የምትኖረው ሊንቲና አንድ ጋኔን ወይም መጥፎ መንፈስ ከቤተሰቧ ውስጥ 16ቱን እንደገደለባትና እሷንም ለ18 ዓመታት በአካልና በአእምሮ እንዳሠቃያት ትናገራለች። ከራሷ ተሞክሮ በመነሣት አጋንንት “እሺ የማይሏቸውን ሰዎች እስከሞት ድረስ በማሠቃየት እንደሚደሰቱ” ትናገራለች።

ይሁን እንጂ ይሖዋ አገልጋዮቹን ከሰይጣን ጥቃቶች ሊጠብቃቸው ይችላል።—ምሳሌ 18:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ