ትሕትና
ይሖዋ ለትሑታን ምን አመለካከት አለው? ለትዕቢተኞችስ?
መዝ 138:6፤ ምሳሌ 15:25፤ 16:18, 19፤ 22:4፤ 1ጴጥ 5:5
በተጨማሪም ምሳሌ 29:23፤ ኢሳ 2:11, 12ን ተመልከት
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
2ዜና 26:3-5, 16-21—ንጉሥ ዖዝያ ታበየ፤ የአምላክን ሕግ የጣሰ ከመሆኑም ሌላ ምክር ሲሰጠው ተቆጣ፤ በዚህም የተነሳ አምላክ በሥጋ ደዌ መታው
ሉቃስ 18:9-14—ይሖዋ ትዕቢተኞች ስለሚያቀርቡት ጸሎትና ትሑታን ስለሚያቀርቡት ጸሎት ምን እንደሚሰማው ኢየሱስ በምሳሌ አስረድቷል
አንድ ሰው ራሱን ዝቅ አድርጎ ከልቡ ንስሐ ሲገባ ይሖዋ ምን ምላሽ ይሰጣል?
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
2ዜና 12:5-7—ንጉሥ ሮብዓምና የይሁዳ መኳንንት በይሖዋ ፊት ራሳቸውን ዝቅ በማድረጋቸው ከጥፋት ድነዋል
2ዜና 32:24-26—ጥሩው ንጉሥ ሕዝቅያስ ታበየ፤ ሆኖም ራሱን ዝቅ በማድረጉ ይሖዋ ይቅርታ አደረገለት
ትሕትና ከሌሎች ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል የሚረዳን እንዴት ነው?
ኤፌ 4:1, 2፤ ፊልጵ 2:3፤ ቆላ 3:12, 13
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 33:3, 4—ኤሳው ወንድሙን ያዕቆብን ይጠላው ነበር፤ ያዕቆብ ግን ወንድሙን ባገኘው ወቅት ታላቅ ትሕትና በማሳየቱ በመካከላቸው ሰላም ሊወርድ ችሏል
መሳ 8:1-3—መስፍኑ ጌድዮን የኤፍሬም ሰዎችን ከእሱ እንደሚሻሉ በትሕትና ነገራቸው፤ ይህም ቁጣቸውን ያበረደው ከመሆኑም ሌላ ግጭት እንዳይፈጠር አድርጓል
ኢየሱስ ትሕትና ያለውን ትልቅ ዋጋ ያስተማረው እንዴት ነው?
ማቴ 18:1-5፤ 23:11, 12፤ ማር 10:41-45
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ኢሳ 53:7፤ ፊልጵ 2:7, 8—በትንቢት በተነገረው መሠረት ኢየሱስ ምድር ላይ የተሰጠውን ኃላፊነት በትሕትና ተቀብሏል፤ ተሠቃይቶና ተዋርዶ ለመሞትም እንኳ ፈቃደኛ ሆኗል
ሉቃስ 14:7-11—ኢየሱስ ትሕትና ያለውን ጥቅም ለማስረዳት በድግስ ቤት ቦታ ስለሚመርጡ ሰዎች ምሳሌ ተናግሯል
ዮሐ 13:3-17—ኢየሱስ ራሱን ዝቅ አድርጎ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ለተከታዮቹ የትሕትና ምሳሌ ትቷል