የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 28, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 3 እስከ የካቲት 28, 2011 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ሕዝቅያስ፣ በነገሠ በመጀመሪያው ወር ምን ሥራ እንዲከናወን አደረገ? እኛስ እሱን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? (2 ዜና 29:16-18) [w09 6/15 ገጽ 9 አን. 13]
2. በኤርምያስ 25:8-11 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ትንቢት ፍጻሜ ማግኘቱን 2 ዜና መዋዕል 36:21 አጉልቶ የሚያሳየው እንዴት ነው? [w06 11/15 ገጽ 32 አን. 1-4]
3. ዕዝራ 3:1-6 ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና የቆየችባቸው 70ዎቹ ዓመታት በተባለው ጊዜ ማብቃቱን የሚገልጸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ የሚደግፈው እንዴት ነው? [w06 1/15 ገጽ 19 አን. 2]
4. ዕዝራ ሕዝቡ በምድሪቱ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በጋብቻ መጣመሩን ሲረዳ የደነገጠው ለምንድን ነው? (ዕዝራ 9:1-3) [w06 1/15 ገጽ 20 አን. 1]
5. ‘መኳንንቶች’ የተባሉት እነማን ናቸው? የትኛው ባሕርያቸው እንዳይጋባብን መጠንቀቅ ይኖርብናል? (ነህ. 3:5) [w06 2/1 ገጽ 9 አን. 10፤ w86-E 2/15 ገጽ 25]
6. ገዥው ነህምያ ለክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ግሩም ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ነህ. 5:14-19) [bsi06 ገጽ 8 አን. 16]
7. በነህምያ ዘመን የነበሩት እስራኤላውያን እንዳደረጉት ‘የአምላካችንን ቤት’ ችላ ከማለት መቆጠብ የምንችለው እንዴት ነው? (ነህ. 10:32-39) [w98 10/15 ገጽ 21-22 አን. 12]
8. በነህምያ ታሪክ ላይ ማሰላሰላችን ራሳችንን ምን ብለን እንድንጠይቅ ሊያነሳሳን ይችላል? (ነህ. 13:31) [w96 9/15 ገጽ 16-17 አን. 3]
9. አስቴር ከንጉሥ ጠረክሲስ ጋር የፆታ ብልግና ፈጽማ ነበር? (አስ. 2:14-17) [w06 3/1 ገጽ 9 አን. 3፤w91 1/1 ገጽ 31 አን. 6]
10. መርዶክዮስ ለሐማ ለመስገድ ፈቃደኛ ያልነበረው ለምንድን ነው? (አስ. 3:2, 4) [w06 3/1 ገጽ 9 አን. 4፤ it-2-E ገጽ 431 አን. 7]