የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 28, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
ዮሴፍ፣ የጲጢፋራ ሚስት ከእሷ ጋር የፆታ ብልግና እንዲፈጽም በጠየቀችው ወቅት እንዲሸሽ የረዳው ምንድን ነው? (ዘፍ. 39:7-12) [መጋ. 3, w13 2/15 ገጽ 4 አን. 6፤ w07 10/15 ገጽ 23 አን. 16]
ዮሴፍ፣ ግፍና የተለያዩ መከራዎች ለሚደርሱባቸው ሰዎች ግሩም ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ዘፍ. 41:14, 39, 40) [መጋ. 10, w04 1/15 ገጽ 29 አን. 6፤ w04 6/1 ገጽ 20 አን. 4]
ዮሴፍ ለወንድሞቹ ምሕረት እንዲያደርግላቸው የሚያነሳሳው ምን በቂ ምክንያት ነበረው? [መጋ. 17, w99 1/1 ገጽ 30 አን. 6-7]
የብንያም ነገድ በዘፍጥረት 49:27 ላይ የሚገኘው ትንቢት እንዲፈጸም ያደረገው እንዴት ነው? [መጋ. 24, w12 1/1 ገጽ 29፣ ሣጥን]
ዘፀአት 3:7-10 ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል? [መጋ. 31, w09 3/1 ገጽ 15 አን. 3-6]
በሙሴ ዘመን ይሖዋ፣ “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” ከሚለው የስሙ ትርጉም ጋር የሚስማማ ነገር ያደረገው እንዴት ነው? (ዘፀ. 3:14, 15) [መጋ. 31, w13 3/15 ገጽ 25-26 አን. 5-6]
በዘፀአት 7:1 ላይ በተገለጸው መሠረት ሙሴ “ለፈርዖን እንደ አምላክ” የሆነው እንዴት ነው? [ሚያ. 7, w04 3/15 ገጽ 25 አን. 7]
እስራኤላውያን፣ ይሖዋ በታላቅ ኃይል ከግብፃውያን እጅ እንዴት እንዳዳናቸው በገዛ ዓይናቸው ቢመለከቱም ከጊዜ በኋላ ምን ዓይነት አመለካከት አዳብረዋል? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘፀ. 14:30, 31) [ሚያ. 14, w12 3/15 ገጽ 26-27 አን. 8-10]
“በንስርም ክንፍ ተሸክሜ” የሚለው አገላለጽ ይሖዋ አዲስ የተቋቋመውን የእስራኤል ብሔር በፍቅር የመራበትን መንገድ በትክክል የሚገልጽ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (ዘፀ. 19:4) [ሚያ. 28, w96 6/15 ገጽ 10 አን. 5 እስከ ገጽ 11 አን. 2]
ይሖዋ ‘በአባቶች ኃጢአት የተነሳ’ ቀጣዮቹን ትውልዶች ‘የሚቀጣው’ እንዴት ነው? (ዘፀ. 20:5) [ሚያ. 28, w04 3/15 ገጽ 27 አን. 1]