መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
109 የማወድስህ አምላክ ሆይ፣+ ዝም አትበል።
2 ክፉዎችና አታላዮች በእኔ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉና።
4 ፍቅር ሳሳያቸው በምላሹ ይቃወሙኛል፤+
እኔ ግን መጸለዬን እቀጥላለሁ።
5 ለመልካም ነገር ክፋትን፣
ላሳየኋቸው ፍቅር ጥላቻን ይመልሱልኛል።+
6 በእሱ ላይ ክፉ ሰው እዘዝበት፤
በቀኙም ተቃዋሚ* ይቁም።
9 ልጆቹ* ያለአባት ይቅሩ፤
ሚስቱም መበለት ትሁን።
10 ልጆቹ* በየቦታው የሚቅበዘበዙ ለማኞች ይሁኑ፤
ከፈራረሰው መኖሪያቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ይንከራተቱ።
11 ያበደረው ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ይውሰድበት፤*
ባዕድ ሰዎችም ንብረቱን ይዝረፉት።
12 ደግነት* የሚያሳየው ሰው ከቶ አይኑር፤
ያለአባት ለቀሩት ልጆቹ የሚራራ አንድም ሰው አይገኝ።
14 አባቶቹ የሠሩትን በደል ይሖዋ አይርሳ፤+
የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ።
15 ይሖዋ የሠሩትን ነገር ምንጊዜም ያስብ፤
መታሰቢያቸውንም ከምድር ገጽ ያጥፋ።+
17 ሌሎችን መርገም ወደደ፤ በመሆኑም እርግማኑ በእሱ ላይ ደረሰበት፤
ሌሎችን ለመባረክ ፍላጎት አልነበረውም፤ ስለዚህ ምንም በረከት አላገኘም።
18 እርግማንን እንደ ልብስ ለበሰ።
እንደ ውኃም ሰውነቱ ውስጥ ፈሰሰ፤
እንደ ዘይት ወደ አጥንቶቹ ዘለቀ።
19 እርግማኑ እንደሚከናነበው ልብስ፣
ሁልጊዜ እንደሚታጠቀውም ቀበቶ ይሁንለት።+
21 አንተ ግን ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣
ለስምህ ስትል እርዳኝ።+
ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ ታደገኝ።+
23 ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ ጥላ አልፋለሁ፤
እንደ አንበጣ አራግፈው ጣሉኝ።
24 ከመጾሜ የተነሳ ጉልበቶቼ ከዱኝ፤
ሰውነቴ ከሳ፤ እኔም እየመነመንኩ ሄድኩ።*
25 የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ።+
ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።+
26 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳኝ፤
በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።
27 ይህ የአንተ እጅ መሆኑን ይወቁ፤
ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ያደረግከው አንተ እንደሆንክ ይገንዘቡ።
28 እነሱ ይራገሙ፤ አንተ ግን ባርክ።
እነሱ በእኔ ላይ ሲነሱ ለኀፍረት ይዳረጉ፤
አገልጋይህ ግን ሐሴት ያድርግ።
30 አንደበቴ ይሖዋን ከልብ ታወድሰዋለች፤
በብዙ ሕዝቦች ፊት አወድሰዋለሁ።+
31 በእሱ* ላይ ከሚፈርዱት ሊያድነው
በድሃው ቀኝ ይቆማልና።