መዝሙር
147 ያህን አወድሱ!*
ለአምላካችን የውዳሴ መዝሙር መዘመር ጥሩ ነው፤
እሱን ማወደስ ደስ ያሰኛል፤ ደግሞም ተገቢ ነው።+
3 የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል፤
ቁስላቸውን ይፈውሳል።
4 የከዋክብትን ብዛት ይቆጥራል፤
ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+
6 ይሖዋ የዋሆችን ያነሳል፤+
ክፉዎችን ግን መሬት ላይ ይጥላል።
7 ለይሖዋ በምስጋና ዘምሩ፤
ለአምላካችን በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤
8 እሱ ሰማያትን በደመናት ይሸፍናል፤
ለምድር ዝናብ ይሰጣል፤+
በተራሮች ላይ ሣር እንዲበቅል ያደርጋል።+
9 ለእንስሳት እንዲሁም የሚበሉትን ለማግኘት ለሚጮኹ የቁራ ጫጩቶች
ምግብ ይሰጣል።+
11 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እሱን በሚፈሩ፣
ታማኝ ፍቅሩን በሚጠባበቁ ሰዎች ይደሰታል።+
12 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጊ።
ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽን አወድሺ።
13 እሱ የከተማሽን በሮች መወርወሪያዎች ያጠናክራል፤
በውስጥሽ ያሉትን ወንዶች ልጆች ይባርካል።
15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤
ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል።
17 የበረዶውን ድንጋይ እንደ ዳቦ ፍርፋሪ ይወረውራል።+
እሱ የሚልከውን ቅዝቃዜ ማን ሊቋቋም ይችላል?+
18 ቃሉን ይልካል፤ እነሱም ይቀልጣሉ።
ነፋሱ እንዲነፍስ ያደርጋል፤+ ውኃውም ይፈስሳል።
19 ቃሉን ለያዕቆብ፣
ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+
20 ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+
እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም።