መዝሙር
ማህሌት።
ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል።*+
3 ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+
4 ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ።
ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ።+
5 ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤
በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት።
6 በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅ+
በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ።
7 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣
መሬትና* በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ።