ኢሳይያስ
55 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ+ ኑ፤ ወደ ውኃው ኑ!+
እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ!
አዎ፣ ኑና ያለገንዘብ፣ ያለዋጋም የወይን ጠጅና ወተት+ ግዙ።+
2 ምግብ ላልሆነ ነገር ለምን ገንዘባችሁን ታወጣላችሁ?
እርካታ ለማያስገኝ ነገርስ ለምን ገቢያችሁን* ታባክናላችሁ?
3 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ።+
5 እነሆ፣ የማታውቀውን ብሔር ትጠራለህ፤
የማያውቅህ ብሔርም ለአምላክህ ለይሖዋና ለእስራኤል ቅዱስ ሲል
ወደ አንተ ሮጦ ይመጣል፤+
ምክንያቱም እሱ ክብር ያጎናጽፍሃል።+
6 ይሖዋን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት።+
በቅርብም ሳለ ጥሩት።+
8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣
መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና”+ ይላል ይሖዋ።
10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣
ምድርን በማራስ እንድታበቅልና እንድታፈራ፣
ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን እንድትሰጥ ሳያደርግ ወደመጣበት እንደማይመለስ ሁሉ፣
11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ እንዲሁ ይሆናል።+
13 በቁጥቋጦ ፋንታ የጥድ ዛፍ ይበቅላል፤+
በሳማም ፋንታ የአደስ ዛፍ ይበቅላል።