የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መኃልየ መኃልይ 6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መኃልየ መኃልይ የመጽሐፉ ይዘት

    • ሱላማዊቷ በኢየሩሳሌም (3:6–8:4)

መኃልየ መኃልይ 6:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:7፤ 2:16

መኃልየ መኃልይ 6:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 7:10
  • +መኃ 2:16

መኃልየ መኃልይ 6:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውብ ከተማ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:17፤ 15:33
  • +መኃ 1:9
  • +መዝ 48:2
  • +መኃ 6:10

መኃልየ መኃልይ 6:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:15፤ 4:9፤ 7:4
  • +መኃ 4:1-3

መኃልየ መኃልይ 6:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

መኃልየ መኃልይ 6:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:1

መኃልየ መኃልይ 6:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የጠራች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 2:14

መኃልየ መኃልይ 6:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ታች የምትመለከት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 6:4

መኃልየ መኃልይ 6:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በደረቁ ወንዝ።”

  • *

    ወይም “አቆጥቁጦ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 2:5

መኃልየ መኃልይ 6:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ።”

  • *

    ወይም “ፈቃደኛ የሆኑ።”

መኃልየ መኃልይ 6:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሁለት ቡድኖች ጭፈራ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መኃ 1:6

ተዛማጅ ሐሳብ

መኃ. 6:2መኃ 1:7፤ 2:16
መኃ. 6:3መኃ 7:10
መኃ. 6:3መኃ 2:16
መኃ. 6:41ነገ 14:17፤ 15:33
መኃ. 6:4መኃ 1:9
መኃ. 6:4መዝ 48:2
መኃ. 6:4መኃ 6:10
መኃ. 6:5መኃ 1:15፤ 4:9፤ 7:4
መኃ. 6:5መኃ 4:1-3
መኃ. 6:81ነገ 11:1
መኃ. 6:9መኃ 2:14
መኃ. 6:10መኃ 6:4
መኃ. 6:11መክ 2:5
መኃ. 6:13መኃ 1:6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መኃልየ መኃልይ 6:1-13

መኃልየ መኃልይ

6 “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣

ውድሽ የት ሄደ?

ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?

አብረንሽ እንፈልገው።”

 2 “ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትና

አበቦችን ለመቅጠፍ

የቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበት

ወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።+

 3 እኔ የውዴ ነኝ፤

ውዴም የእኔ ነው።+

እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።”+

 4 “ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ*+ ቆንጆ ነሽ፤+

እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤+

በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ።+

 5 ስሜቴን አውከውታልና፣

ዓይኖችሽን+ ከእኔ ላይ አንሺ።

ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድ

የፍየል መንጋ ነው።+

 6 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣

ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ

የበግ መንጋ ናቸው፤

ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም።

 7 በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*

የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

 8 እርግጥ 60 ንግሥቶች፣

80 ቁባቶችና

ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ።+

 9 እንከን የሌለባት ርግቤ+ ግን አንድ ብቻ ናት።

እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት።

በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ* ናት።

ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤

ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል።

10 ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣*

እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣

እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣

በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’”+

11 “በሸለቆው* ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣

ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣*

የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከት

የገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ።+

12 ምንም ሳይታወቀኝ

ምኞቴ* የተከበሩ* ወገኖቼ

የያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።”

13 “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ!

እናይሽ ዘንድ

ተመለሺ፤ ተመለሺ!”

“በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?”+

“እሷ የመሃናይምን ጭፈራ* ትመስላለች!”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ