ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ማስኪል። የዳዊት መዝሙር፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል ሄዶ፣ ዳዊት ወደ አሂሜሌክ ቤት መጥቶ እንደነበር በነገረው ጊዜ።+
52 አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?+
የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም?+
2 ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤+
ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል።+
3 መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣
ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ)
4 አንተ አታላይ ምላስ!
ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ።
5 በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤+
መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤+
ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል።+ (ሴላ)
6 ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት ይዋጣሉ፤+
በእሱም ላይ ይስቃሉ።+
7 “እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው አያደርግም፤+
ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤+
ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ ይመካል።”
8 እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤
ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ።+
9 እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤+
መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊት
በስምህ ተስፋ አደርጋለሁ።+