የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 39:7-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 በኋላም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጣለችበት፤ እሷም “ከእኔ ጋር ተኛ” ትለው ጀመር። 8 እሱ ግን ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ የጌታውን ሚስት እንዲህ አላት፦ “ጌታዬ በዚህ ቤት በእኔ እጅ ስላለው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውንም ነገር ሁሉ በአደራ ሰጥቶኛል። 9 በዚህ ቤት ውስጥ ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ጌታዬ ከአንቺ በስተቀር ምንም ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ ይህን ያደረገውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን እጅግ መጥፎ ድርጊት በመፈጸም በአምላክ ላይ እንዴት ኃጢአት እሠራለሁ?”+

  • ዘዳግም 5:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 “‘አታመንዝር።+

  • ምሳሌ 6:32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 ከሴት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሁሉ ማስተዋል* ይጎድለዋል፤

      እንዲህ የሚያደርግ ሰው በራሱ* ላይ ጥፋት ያመጣል።+

  • ማቴዎስ 5:27, 28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 “‘አታመንዝር’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። 28 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ አንዲትን ሴት በፍትወት ስሜት የሚመለከት+ ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል።+

  • ሮም 13:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል።

  • 1 ቆሮንቶስ 6:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ከፆታ ብልግና* ሽሹ!+ አንድ ሰው የሚፈጽመው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ የፆታ ብልግና የሚፈጽም ሁሉ ግን በራሱ አካል ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው።+

  • ዕብራውያን 13:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤+ አምላክ ሴሰኞችንና* አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ