ዘፀአት 21:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል።+ ዘሌዋውያን 19:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤*+ ሰንበቶቼንም ይጠብቅ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ዘዳግም 27:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) ምሳሌ 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤+የእናትህንም መመሪያ* አትተው።+ ማርቆስ 7:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ለምሳሌ ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ* ይገደል’+ ብሏል።