ዘፀአት 20:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “አትስረቅ።+ ዘሌዋውያን 19:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። ምሳሌ 30:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+ ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+ 9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ። 1 ቆሮንቶስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ ኤፌሶን 4:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 የሚሰርቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ከዚህ ይልቅ ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።+
8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+ ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+ 9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ።