ዘሌዋውያን 19:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። ዘዳግም 5:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “‘አትስረቅ።+ ማርቆስ 10:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ‘አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ አታታል፣+ አባትህንና እናትህን አክብር’+ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ ኤፌሶን 4:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 የሚሰርቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ከዚህ ይልቅ ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።+
9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+