የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 28:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+

  • ዘዳግም 28:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 “ይሖዋ በፈጸምካቸው መጥፎ ድርጊቶችና እኔን በመተውህ የተነሳ ፈጥነህ እስክትደመሰስ እንዲሁም እስክትጠፋ ድረስ፣ በምታከናውነው በማንኛውም ሥራ ላይ እርግማንን፣ ግራ መጋባትንና ቅጣትን ያመጣብሃል።+

  • ኢያሱ 23:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ካፈረሳችሁ እንዲሁም ሄዳችሁ ሌሎች አማልክትን ካገለገላችሁና ለእነሱ ከሰገዳችሁ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤+ ከሰጣችሁም መልካም ምድር ላይ በፍጥነት ትጠፋላችሁ።”+

  • 2 ዜና መዋዕል 15:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 እሱም ከአሳ ጋር ለመገናኘት ወጥቶ እንዲህ አለው፦ “አሳ ሆይ፣ ይሁዳና ቢንያም ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእሱ ጋር እስከሆናችሁ ድረስ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤+ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤+ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።+

  • ኢሳይያስ 63:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 እነሱ ግን ዓመፁ፤+ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ።+

      በዚህ ጊዜ ጠላት ሆነባቸው፤+

      ደግሞም ተዋጋቸው።+

  • ኤርምያስ 17:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣

      አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ።

      አንተን* የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤+

      ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ