መሳፍንት 3:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። መሳፍንት 6:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤* + እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤+ አቢዔዜራውያንም+ እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። መሳፍንት 11:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ። መሳፍንት 14:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም። 1 ሳሙኤል 10:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በመሆኑም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታው ሄዱ፤ አንድ የነቢያት ቡድንም አገኘው። ወዲያውም የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እሱም አብሯቸው ትንቢት መናገር ጀመረ።+ 11 ቀደም ሲል ያውቁት የነበሩት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ሆኖ ትንቢት ሲናገር ሲያዩት እርስ በርሳቸው “የቂስ ልጅ ምን ሆኗል? ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ?” ተባባሉ። 1 ሳሙኤል 16:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ።
9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት።
29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ።
5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም።
10 በመሆኑም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታው ሄዱ፤ አንድ የነቢያት ቡድንም አገኘው። ወዲያውም የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እሱም አብሯቸው ትንቢት መናገር ጀመረ።+ 11 ቀደም ሲል ያውቁት የነበሩት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ሆኖ ትንቢት ሲናገር ሲያዩት እርስ በርሳቸው “የቂስ ልጅ ምን ሆኗል? ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ?” ተባባሉ።
13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ።