መሳፍንት 3:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። መሳፍንት 11:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ። መሳፍንት 13:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በኋላም ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን+ አለችው፤ ልጁም እያደገ ሄደ፤ ይሖዋም ባረከው። 25 ከጊዜ በኋላም በጾራ እና በኤሽታዖል+ መካከል በምትገኘው በማሃነህዳን+ ሳለ የይሖዋ መንፈስ ይገፋፋው ጀመር።+ መሳፍንት 14:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም። መሳፍንት 15:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እሱም ሊሃይ ሲደርስ ፍልስጤማውያኑ እሱን በማግኘታቸው በድል አድራጊነት ጮኹ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እጆቹ የታሰሩባቸውም ገመዶች እሳት እንደበላው የበፍታ ክር ሆኑ፤ ማሰሪያዎቹም ከእጆቹ ላይ ቀልጠው ወደቁ።+ ዘካርያስ 4:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣+ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት።
29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ።
24 በኋላም ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን+ አለችው፤ ልጁም እያደገ ሄደ፤ ይሖዋም ባረከው። 25 ከጊዜ በኋላም በጾራ እና በኤሽታዖል+ መካከል በምትገኘው በማሃነህዳን+ ሳለ የይሖዋ መንፈስ ይገፋፋው ጀመር።+
6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም።
14 እሱም ሊሃይ ሲደርስ ፍልስጤማውያኑ እሱን በማግኘታቸው በድል አድራጊነት ጮኹ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እጆቹ የታሰሩባቸውም ገመዶች እሳት እንደበላው የበፍታ ክር ሆኑ፤ ማሰሪያዎቹም ከእጆቹ ላይ ቀልጠው ወደቁ።+
6 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣+ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።