መሳፍንት 3:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። መሳፍንት 6:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤* + እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤+ አቢዔዜራውያንም+ እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። መሳፍንት 11:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ። 1 ሳሙኤል 11:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሳኦልም ይህን ሲሰማ የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ ቁጣውም ነደደ።
9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ 10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት።
29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ።