-
2 ዜና መዋዕል 2:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ለእሱ ቤት መሥራት የሚችል ማነው? ሰማያትና የሰማያት ሰማይ ሊይዙት አይችሉምና፤+ በፊቱ የሚጨስ መሥዋዕት የሚቀርብበት ስፍራ ካልሆነ በስተቀር ለእሱ ቤት እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
-
-
2 ዜና መዋዕል 6:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “በእርግጥ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር በምድር ላይ ይኖራል?+ እነሆ ሰማያት፣ አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ ሊይዙህ አይችሉም፤+ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤትማ ምንኛ ያንስ!+ 19 እንግዲህ አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመና በትኩረት ስማ፤ አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰማውን ጩኸትና በፊትህ የሚያቀርበውን ጸሎት አዳምጥ። 20 አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ስምህ እንደሚጠራበት+ ወደተናገርከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ሌሊትና ቀን ይመልከቱ። 21 አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመናና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልይበት ጊዜ+ የሚያቀርበውን ልመና አዳምጥ፤ በማደሪያህም በሰማያት ሆነህ ስማ፤+ ሰምተህም ይቅር በል።+
-