የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 14:2-5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 አሳ በአምላኩ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ። 3 የባዕድ አማልክቱን መሠዊያዎችና+ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች አስወገደ፤ የማምለኪያ ዓምዶቹንም ሰባበረ፤+ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቹን* ቆራረጠ።+ 4 በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን እንዲፈልጉ እንዲሁም ሕጉንና ትእዛዙን እንዲያከብሩ አዘዘ። 5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የዕጣን ማጨሻዎቹን አስወገደ፤+ መንግሥቱም በእሱ አገዛዝ ሥር ሰላም አገኘ።

  • 2 ዜና መዋዕል 14:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ የምትረዳው ሕዝብ ብዛት ያለውም ይሁን ደካማ ለአንተ የሚያመጣው ለውጥ የለም።+ ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ እርዳን፤ በአንተ ታምነናልና፤*+ በስምህ ይህን ታላቅ ሠራዊት ለመግጠም ወጥተናል።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህ። ሟች የሆነ ሰው በአንተ ላይ አይበርታ።”+

  • 2 ዜና መዋዕል 15:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን ከእስራኤል አልተወገዱም ነበር።+ ይሁንና አሳ በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ በሙሉ ልቡ ተመላልሷል።*+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ