የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 17:15, 16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ስለሆነም ሄዳ ኤልያስ እንዳላት አደረገች፤ እሷም ሆነች እሱ እንዲሁም ቤተሰቧ ለብዙ ቀናት ሲመገቡ ቆዩ።+ 16 ይሖዋ በኤልያስ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም።

  • 1 ነገሥት 17:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+

  • 1 ነገሥት 17:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን “አንተ በእርግጥ የአምላክ ሰው+ እንደሆንክ በአንደበትህም ያለው የይሖዋ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅኩ” አለችው።

  • 1 ነገሥት 18:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ነቢዩ ኤልያስም የምሽቱ የእህል መባ በሚቀርብበት ጊዜ+ ገደማ ወደ ፊት ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፦ “የአብርሃም፣+ የይስሐቅና+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእስራኤል ውስጥ አምላክ እንደሆንክ፣ እኔም አገልጋይህ እንደሆንኩና እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግኩት በአንተ ቃል እንደሆነ ዛሬ ይታወቅ።+

  • 1 ነገሥት 18:38
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 38 በዚህ ጊዜ የይሖዋ እሳት ወርዶ የሚቃጠለውን መባ፣ እንጨቱን፣ ድንጋዮቹንና አፈሩን በላ፤+ በቦዩ ውስጥ የነበረውንም ውኃ ላሰ።+

  • 1 ነገሥት 18:46
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 46 ሆኖም የይሖዋ እጅ በኤልያስ ላይ መጣ፤ እሱም ልብሱን ጠቅልሎ መቀነቱ ውስጥ በመሸጎጥ* ከአክዓብ ፊት ፊት እየሮጠ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ ሄደ።

  • 2 ነገሥት 2:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ከዚያም ኤልያስ የነቢይ ልብሱን+ አውልቆ በመጠቅለል ውኃውን መታው፤ ውኃውም ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+

  • 2 ነገሥት 2:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ሁለቱ እየተጨዋወቱ በመሄድ ላይ ሳሉ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች+ ድንገት መጥተው ለያዩአቸው፤ ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ወደ ሰማይ ወጣ።+

  • ሉቃስ 1:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ * ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣*+ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል+ በአምላክ ፊት ይሄዳል።”+

  • ዮሐንስ 1:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 አይሁዳውያን “አንተ ማን ነህ?”+ ብለው እንዲጠይቁት ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩ ጊዜ ዮሐንስ የሰጠው ምሥክርነት ይህ ነው፤

  • ዮሐንስ 1:21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 እነሱም “ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህ?”+ ሲሉ ጠየቁት። እሱም መልሶ “አይደለሁም” አለ። “ነቢዩ ነህ?”+ አሉት። እሱም “አይደለሁም!” ሲል መለሰ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ