2 ሳሙኤል 2:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሦስቱ የጽሩያ+ ልጆች ኢዮዓብ፣+ አቢሳ+ እና አሳሄል+ እዚያ ነበሩ፤ አሳሄል በመስክ ላይ እንዳለች የሜዳ ፍየል ፈጣን ሯጭ ነበር። 2 ሳሙኤል 3:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በመሆኑም ኢዮዓብና ወንድሙ አቢሳ+ በገባኦን በተደረገው ውጊያ ላይ ወንድማቸውን አሳሄልን ስለገደለባቸው+ አበኔርን+ ገደሉት። 2 ሳሙኤል 23:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የኢዮዓብ ወንድም አሳሄል+ ከሠላሳዎቹ አንዱ ነበር፤ ከኃያላኑ ሰዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የቤተልሔሙ+ የዶዶ ልጅ ኤልሃናን፣