ዘፀአት 34:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና+ ሩኅሩኅ*+ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣+ ታማኝ ፍቅሩና*+ እውነቱ*+ እጅግ ብዙ የሆነ፣ መዝሙር 51:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 አምላክ ሆይ፣ እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን ሞገስ አሳየኝ።+ እንደ ታላቅ ምሕረትህ መተላለፌን ደምስስ።+ ኢሳይያስ 55:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤+ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና።+
6 ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና+ ሩኅሩኅ*+ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣+ ታማኝ ፍቅሩና*+ እውነቱ*+ እጅግ ብዙ የሆነ፣