1 ነገሥት 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ።+ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን+ ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ።+ 1 ነገሥት 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አምላክም ለሰለሞን እጅግ ታላቅ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም በባሕር ዳርቻ ላይ እንዳለ አሸዋ፣ ሰፊ ልብ* ሰጠው።+ ኢዮብ 35:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከምድር እንስሳት+ ይበልጥ እኛን ያስተምረናል፤+በሰማይ ከሚበርሩ ወፎችም በላይ ጥበበኞች አድርጎናል። ምሳሌ 2:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤+ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል። መክብብ 2:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 አምላክ እሱን ለሚያስደስት ሰው ጥበብ፣ እውቀትና ደስታ ይሰጣል፤+ ኃጢአተኛ ለሆነው ግን እውነተኛውን አምላክ ለሚያስደስት ሰው ይሰጥ ዘንድ የመሰብሰብና የማከማቸት ሥራ ሰጥቶታል።+ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። ዳንኤል 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እውነተኛው አምላክም ለእነዚህ አራት ወጣቶች* በሁሉም ዓይነት የጽሑፍና የጥበብ መስክ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ሁሉንም ዓይነት ራእዮችና ሕልሞች የመረዳት ችሎታ ተሰጠው።+ ማቴዎስ 11:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+ ያዕቆብ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+
26 አምላክ እሱን ለሚያስደስት ሰው ጥበብ፣ እውቀትና ደስታ ይሰጣል፤+ ኃጢአተኛ ለሆነው ግን እውነተኛውን አምላክ ለሚያስደስት ሰው ይሰጥ ዘንድ የመሰብሰብና የማከማቸት ሥራ ሰጥቶታል።+ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው።
17 እውነተኛው አምላክም ለእነዚህ አራት ወጣቶች* በሁሉም ዓይነት የጽሑፍና የጥበብ መስክ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ሁሉንም ዓይነት ራእዮችና ሕልሞች የመረዳት ችሎታ ተሰጠው።+
25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+
5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+