ዘዳግም 5:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ምንጊዜም እኔን የሚፈራና+ ትእዛዛቴን ሁሉ የሚጠብቅ ልብ+ ቢኖራቸው ምናለ፤ እንዲህ ቢሆን ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም ይሆንላቸው ነበር!+ ኢሳይያስ 48:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ “የሚጠቅምህን ነገር* የማስተምርህ፣+ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ 18 ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው!+ እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣+ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።+
17 የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ “የሚጠቅምህን ነገር* የማስተምርህ፣+ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ 18 ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው!+ እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣+ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።+