2 ሳሙኤል 7:12-15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+ 15 ከፊትህ ካስወገድኩት ከሳኦል ላይ ታማኝ ፍቅሬን እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አይወሰድም። መዝሙር 132:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦ “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+ ኢሳይያስ 55:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ።+ አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤*ለዳዊት ካሳየሁት የማይከስም * ታማኝ ፍቅር+ ጋር በሚስማማ ሁኔታከእናንተ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+
12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+ 15 ከፊትህ ካስወገድኩት ከሳኦል ላይ ታማኝ ፍቅሬን እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አይወሰድም።
3 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ።+ አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤*ለዳዊት ካሳየሁት የማይከስም * ታማኝ ፍቅር+ ጋር በሚስማማ ሁኔታከእናንተ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+