-
ዘፀአት 16:12-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “የእስራኤላውያንን ማጉረምረም ሰምቻለሁ።+ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አመሻሹ ላይ* ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ላይ ደግሞ ዳቦ ትጠግባላችሁ፤+ እኔም አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ።’”+
13 በዚህም መሠረት ምሽት ላይ ድርጭቶች መጥተው ሰፈሩን አለበሱት፤+ ጠዋት ላይም በሰፈሩ ውስጥ ሁሉ ጤዛ ወርዶ ነበር። 14 በኋላም ጤዛው ሲተን በምድረ በዳው ላይ እንደ አመዳይ ደቃቅ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ስስ ነገር+ መሬቱ ላይ ታየ። 15 እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው።+
-