ዘዳግም 15:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* መዝሙር 41:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል። ምሳሌ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ ሉቃስ 6:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እንዲሁም ይመልስልኛል ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ብታበድሩ* ምን ፋይዳ አለው?+ ኃጢአተኞችም እንኳ የሰጡትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኃጢአተኞች ያበድራሉ። 35 ከዚህ ይልቅ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ደግሞም በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ አበድሩ፤+ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፤ ደግሞም የልዑሉ አምላክ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ደግ ነውና።+ የሐዋርያት ሥራ 20:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤+ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’+ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።” ዕብራውያን 13:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤+ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና።+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።*
34 እንዲሁም ይመልስልኛል ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ብታበድሩ* ምን ፋይዳ አለው?+ ኃጢአተኞችም እንኳ የሰጡትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኃጢአተኞች ያበድራሉ። 35 ከዚህ ይልቅ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ደግሞም በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ አበድሩ፤+ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፤ ደግሞም የልዑሉ አምላክ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ደግ ነውና።+
35 እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤+ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’+ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።”