ዘፀአት 33:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እባክህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንድኖር መንገድህን አሳውቀኝ።+ እንዲሁም ይህ ብሔር ሕዝብህ እንደሆነ አስብ።”+ መዝሙር 86:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ።+ በእውነትህ እሄዳለሁ።+ ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ።*+ መዝሙር 143:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ። ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣*ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+