መዝሙር 25:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አሳውቀኝ፤+ጎዳናህንም አስተምረኝ።+ መዝሙር 27:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ። መዝሙር 86:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ።+ በእውነትህ እሄዳለሁ።+ ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ።*+ መዝሙር 119:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይሖዋ ሆይ፣ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፤+እኔም እስከ መጨረሻው እከተለዋለሁ።+ ኢሳይያስ 30:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብትል ጆሮህ ከኋላህ “መንገዱ ይህ ነው።+ በእሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።+