የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 23:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣

      የእስራኤል ዓለት+ እንዲህ አለኝ፦

      ‘የሰው ልጆችን የሚገዛው ጻድቅ ሲሆን፣+

      አምላክን በመፍራት ሲገዛ፣+

       4 ፀሐይ በምትፈነጥቅበት ጊዜ እንደሚኖረው የማለዳ ብርሃን፣+

      ደመና እንደሌለበት ማለዳ ይሆናል።

      ሣርን ከምድር እንደሚያበቅል፣+

      ዝናብ ካባራ በኋላ ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የፀሐይ ብርሃን ነው።’

  • መዝሙር 119:105
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 105 ቃልህ ለእግሬ መብራት፣

      ለመንገዴም ብርሃን ነው።+

  • 1 ቆሮንቶስ 13:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 አሁን በብረት መስተዋት ብዥ ያለ* ምስል ይታየናል፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት የማየት ያህል በግልጽ ይታየናል። አሁን ስለ አምላክ የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እሱ እኔን በትክክል የሚያውቀኝን ያህል የተሟላ* እውቀት ይኖረኛል።

  • 2 ቆሮንቶስ 4:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 “በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይብራ” ያለው አምላክ ነውና፤+ ስለሆነም በክርስቶስ ፊት አማካኝነት፣ በልባችን ውስጥ ስለ አምላክ አስደናቂ እውቀት ይፈነጥቅ ዘንድ በልባችን ላይ ብርሃን አብርቷል።+

  • 2 ጴጥሮስ 1:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 በመሆኑም ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ጎህ እስኪቀድና የንጋት ኮከብ+ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ቦታ፣ በልባችሁ ውስጥ ለሚበራ መብራት+ የምትጠነቀቁትን ያህል ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት መስጠታችሁ መልካም ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ