የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 21:20, 21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 አክዓብም ኤልያስን “ጠላቴ ሆይ፣ አገኘኸኝ?” አለው፤+ እሱም እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ አግኝቼሃለሁ። ‘እንግዲህ አንተ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጠህ ስለተነሳህ*+ 21 ጥፋት አመጣብሃለሁ፤ እየተከታተልኩም ሙልጭ አድርጌ እጠርግሃለሁ፤ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን+ ጨምሮ የአክዓብ የሆነውን ወንድ* ሁሉ አጠፋለሁ።+

  • 1 ነገሥት 22:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል፤+ ሆኖም ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ።+ እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥ ግን “ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም” አለ።

  • 2 ዜና መዋዕል 25:15, 16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ስለሆነም የይሖዋ ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይም ልኮ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ መታደግ ያልቻሉትን የሕዝቡን አማልክት የምትከተለው ለምንድን ነው?” አለው።+ 16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ነቢዩን “የንጉሡ አማካሪ አድርገን ሾመንሃል?+ ዝም በል!+ መሞት ትፈልጋለህ?” አለው። ነቢዩም ዝም አለ፤ ሆኖም “ይህን በማድረግህና ምክሬን ባለመስማትህ አምላክ ሊያጠፋህ እንደወሰነ ተረዳሁ” አለ።+

  • ማቴዎስ 7:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 “ቅዱስ የሆነውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በአሳማ ፊት አትጣሉ።+ አለዚያ ዕንቁዎቹን በእግራቸው ይረጋግጧቸዋል፤ ተመልሰውም ይጎዷችኋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ