1 ሳሙኤል 15:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤ 23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት+ ሟርት+ ከመፈጸም አይተናነስም፤ እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ* ተለይቶ አይታይም። አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ+ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም።”+ ሆሴዕ 6:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣*ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና።+ ሚክያስ 6:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል?+ ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም* ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?+ 8 ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣*+ ታማኝነትን እንድትወድና*+ልክህን አውቀህ+ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!+ ማቴዎስ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሁንና ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን+ እንጂ መሥዋዕትን+ አይደለም’ የሚለውን ቃል ትርጉም ተረድታችሁ ቢሆን ኖሮ ምንም በደል ባልሠሩት ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር።
22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤ 23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት+ ሟርት+ ከመፈጸም አይተናነስም፤ እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ* ተለይቶ አይታይም። አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ+ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም።”+
7 ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል?+ ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም* ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?+ 8 ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣*+ ታማኝነትን እንድትወድና*+ልክህን አውቀህ+ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!+
7 ይሁንና ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን+ እንጂ መሥዋዕትን+ አይደለም’ የሚለውን ቃል ትርጉም ተረድታችሁ ቢሆን ኖሮ ምንም በደል ባልሠሩት ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር።