ምሳሌ 5:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የሰው መንገድ በይሖዋ ዓይኖች ፊት ነውና፤እሱ መንገዱን ሁሉ ይመረምራል።+ ምሳሌ 17:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው።+ ምሳሌ 21:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤+ይሖዋ ግን ልብን ይመረምራል።*+