ዘፀአት 20:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ።+ 5 አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ ዘሌዋውያን 26:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “‘ትሰግዱላቸው ዘንድ+ ለራሳችሁ ከንቱ አማልክትን አትሥሩ፤+ እንዲሁም ለራሳችሁ የተቀረጸ ምስል+ ወይም የማምለኪያ ዓምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ከድንጋይ የተቀረጸ ምስል አታኑሩ፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ዕንባቆም 2:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+ 19 እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+በውስጡም እስትንፋስ የለም።+
4 “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ።+ 5 አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤
26 “‘ትሰግዱላቸው ዘንድ+ ለራሳችሁ ከንቱ አማልክትን አትሥሩ፤+ እንዲሁም ለራሳችሁ የተቀረጸ ምስል+ ወይም የማምለኪያ ዓምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ከድንጋይ የተቀረጸ ምስል አታኑሩ፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።
18 የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+ 19 እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+በውስጡም እስትንፋስ የለም።+