የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 7:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ።

  • 2 ሳሙኤል 7:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+

  • መዝሙር 132:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤

      የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦

      “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*

      በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+

  • ኢሳይያስ 9:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤

      እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነ

      ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+

      ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

      በማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+

      በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል።

      የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

  • ኢሳይያስ 11:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ከእሴይ+ ጉቶ፣ ቅርንጫፍ ይወጣል፤

      ከሥሮቹም የሚወጣው ቀንበጥ ፍሬ ያፈራል።+

  • ኢሳይያስ 11:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+

      ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+

      ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል።

  • ኤርምያስ 23:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+

  • ማቴዎስ 1:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 1 የዳዊት ልጅ፣+ የአብርሃም ልጅ+ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን* ታሪክ* የያዘ መጽሐፍ፦

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ