ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ መዝሙር 2:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይንጉሤን ሾምኩ።”+ ሉቃስ 1:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+ ዮሐንስ 1:49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 ናትናኤልም “ረቢ፣ አንተ የአምላክ ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” ሲል መለሰለት።+
32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+