-
ኢያሱ 4:21-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ከዚያም እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “ወደፊት ልጆቻችሁ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ+ 22 ልጆቻችሁን እንዲህ በሏቸው፦ ‘እስራኤል ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ተሻገረ፤+ 23 ይህም የሆነው አምላካችሁ ይሖዋ ቀይ ባሕርን እስኪሻገሩ ድረስ ባሕሩን በፊታቸው እንዳደረቀው ሁሉ እኛም ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ ይሖዋ የዮርዳኖስን ውኃ በፊታችን ስላደረቀው ነው።+ 24 ይህን ያደረገው የምድር ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋ ክንድ ምን ያህል ኃያል መሆኑን እንዲያውቁና+ እናንተም አምላካችሁን ይሖዋን ሁልጊዜ እንድትፈሩ ነው።’”
-