2 ነገሥት 21:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+ ኢሳይያስ 59:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እግሮቻቸው ክፋት ለመፈጸም ይሮጣሉ፤ንጹሕ ደም ለማፍሰስም ይጣደፋሉ።+ የሚያስቡት ጎጂ ሐሳብ ነው፤በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።+ ኤርምያስ 2:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+ ማቴዎስ 23:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ 35 በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም+ ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+
16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+
34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ 35 በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም+ ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+