የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 28:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ፍልስጤማውያን+ ደግሞ በይሁዳ የሚገኙትን የሸፌላንና+ የኔጌብን ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽን፣+ አይሎንን፣+ ገዴሮትን፣ ሶኮንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ቲምናንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ጊምዞንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ተቀመጡ።

  • ኢሳይያስ 9:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ የረጺንን ባላጋራዎች በእሱ ላይ ያስነሳል፤

      ጠላቶቹንም እርምጃ እንዲወስዱ ይቀሰቅሳቸዋል፤

      12 ሶርያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጤማውያንን ደግሞ ከምዕራብ* ያመጣበታል፤+

      እነሱም አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይውጡታል።+

      ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤

      ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+

  • ኢሳይያስ 14:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 “ፍልስጤማውያን ሆይ፣ የመቺያችሁ በትር ስለተሰበረ

      አንዳችሁም ብትሆኑ ደስ አይበላችሁ።

      ከእባቡ ሥር+ መርዘኛ እባብ ይወጣልና፤+

      ዘሩም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* ይሆናል።

  • ኤርምያስ 47:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 47 ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።

  • ኢዩኤል 3:4-6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ጢሮስ፣ ሲዶና እና የፍልስጤም ግዛቶች ሁሉ፣

      ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አላችሁ?

      ላደረግኩባችሁ ነገር ብድራት ልትመልሱልኝ ነው?

      ብድራት የምትመልሱልኝ ከሆነ

      ብድራታችሁን ወዲያውኑ፣ በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።+

       5 ምክንያቱም እናንተ ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤+

      እጅግ ምርጥ የሆነውን ውድ ንብረቴንም ወደ ቤተ መቅደሶቻችሁ አስገብታችኋል፤

       6 ደግሞም ከምድራቸው ርቀው እንዲሄዱ ለማድረግ ስትሉ

      የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለግሪኮች ሸጣችሁ፤+

  • አሞጽ 1:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      ‘“ስለ ሦስቱ የጋዛ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤

      ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው+ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ