ኢሳይያስ 55:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ ኤርምያስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ። ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+ “እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+ ኤርምያስ 25:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ። የሐዋርያት ሥራ 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ+ ንስሐ ግቡ፣+ ተመለሱም፤+ ከይሖዋም ዘንድ* የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤
5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ።