ዘዳግም 32:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 ይሖዋ ሕዝቡን ይዳኛል፤+አገልጋዮቹ አቅም እንዳነሳቸው፣ረዳት የለሽና ደካማ የሆኑት ብቻ እንደቀሩ ሲያይለእነሱ ያዝንላቸዋል።*+ ኢሳይያስ 60:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የባዕድ አገር ሰዎች ቅጥሮችሽን ይገነባሉ፤ነገሥታታቸውም ያገለግሉሻል፤+በቁጣዬ መትቼሻለሁና፤በሞገሴ* ግን ምሕረት አሳይሻለሁ።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤+ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና።+ ሆሴዕ 11:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ?+ እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ?+ ስለ አንተ ያለኝ አመለካከት ተለወጠ፤የርኅራኄ ስሜቴም ተቀሰቀሰ።*+
8 ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ?+ እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ?+ ስለ አንተ ያለኝ አመለካከት ተለወጠ፤የርኅራኄ ስሜቴም ተቀሰቀሰ።*+