የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 11:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። 12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+

  • ኢሳይያስ 43:5, 6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+

      ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤

      ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።+

       6 ሰሜንን ‘ልቀቃቸው!’ እለዋለሁ፤+

      ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው።

      ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ አምጣ፤+

  • ኢሳይያስ 49:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 እነሆ፣ እነዚህ ከሩቅ ይመጣሉ፤+

      እነሆም፣ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፣

      እነዚህ ደግሞ ከሲኒም ምድር ይመጣሉ።”+

  • ኤርምያስ 23:7, 8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 “ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!’ የማይሉበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤+ 8 “ከዚህ ይልቅ ‘የእስራኤልን ቤት ዘሮች ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ባወጣውና መልሶ ባመጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ’ ይላሉ፤ እነሱም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”+

  • ሕዝቅኤል 34:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ።+ በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ