የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 28:49, 50
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+

  • 2 ነገሥት 15:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሄ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ ወረራ በማካሄድ ኢዮንን፣ አቤልቤትማዓካን፣+ ያኖአህን፣ ቃዴሽን፣+ ሃጾርን፣ ጊልያድን+ እንዲሁም ገሊላን ይኸውም መላውን የንፍታሌም+ ምድር ያዘ፤ ነዋሪዎቹንም በግዞት ወደ አሦር ወሰደ።+

  • 2 ነገሥት 17:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ።+ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ወደ አሦር በግዞት+ በመውሰድ በሃላህ፣ በጎዛን+ ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+

  • ኢሳይያስ 7:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 “በዚያም ቀን ይሖዋ በወንዙ* አካባቢ ከሚገኘው ቦታ በተከራየው ምላጭ ይኸውም በአሦር ንጉሥ+ አማካኝነት ራሱንና የእግሩን ፀጉር ይላጨዋል፤ ጢሙንም ሙልጭ አድርጎ ያስወግደዋል።

  • ኢሳይያስ 8:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+

  • ኢሳይያስ 10:5, 6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 “የቁጣዬ በትር የሆነውንና+

      ውግዘቴን የምገልጽበትን ዱላ በእጁ የያዘውን

      አሦራዊ+ ተመልከት!

       6 ከሃዲ በሆነው ብሔር ላይ፣

      እጅግ ባስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤+

      ብዙ ምርኮ እንዲወስድ፣ ብዙ ሀብት እንዲዘርፍና

      ሕዝቡን በጎዳናዎች ላይ እንዳለ ጭቃ እንዲረጋግጥ አዘዋለሁ።+

  • ሆሴዕ 10:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል።+

      ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤

      እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ