የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 28:45
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 45 “አምላክህ ይሖዋ ያዘዘህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች ባለመጠበቅ ቃሉን ስላልሰማህ እነዚህ እርግማኖች ሁሉ+ እስክትጠፋ ድረስ ይወርዱብሃል፤+ ያሳድዱሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል።+

  • 2 ነገሥት 17:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ።+ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ወደ አሦር በግዞት+ በመውሰድ በሃላህ፣ በጎዛን+ ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+

      7 ይህ የሆነው የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ቀንበርና ከግብፅ ምድር ነፃ ባወጣቸው በአምላካቸው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ ነው።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን አመለኩ፤*+

  • ሕዝቅኤል 23:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 የታላቂቱ ስም ኦሆላ፣* የእህቷም ስም ኦሆሊባ* ነበር። እነሱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውን በተመለከተ፣ ኦሆላ ሰማርያ+ ስትሆን ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።

      5 “ኦሆላ የእኔ ሆና ሳለች ታመነዝር ጀመር።+ ጎረቤቶቿ የሆኑትን ፍቅረኞቿን+ አሦራውያንን በፍትወት ተመኘች።+

  • ሆሴዕ 4:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣

      ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤+

      ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም።+

       2 የሐሰት መሐላ፣ ውሸት፣+ ነፍስ ግድያ፣+

      ስርቆትና ምንዝር+ ተስፋፍቷል፤

      ደም የማፍሰስ ወንጀልም በላይ በላዩ ይፈጸማል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ