ዘፍጥረት 10:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ኩሽ ናምሩድን ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። ዘፍጥረት 10:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚያ ምድር ተነስቶም ወደ አሦር+ በመሄድ ነነዌን፣+ ረሆቦትኢርን እና ካላህን ቆረቆረ፤ ናሆም 1:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 1 በነነዌ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የኤልቆሻዊው የናሆም* የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፦ ሶፎንያስ 2:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል።+