ኢሳይያስ 1:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+ ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+ አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ* አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።+ ኢሳይያስ 5:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ጥሩውን መጥፎ፣ መጥፎውንም ጥሩ የሚሉ፣+ጨለማውን በብርሃን፣ ብርሃኑን በጨለማ የሚተኩጣፋጩን መራራ፣ መራራውን ጣፋጭ አድርገው የሚያቀርቡ ወዮላቸው! ኢሳይያስ 5:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ጉቦ በመቀበል ክፉውን ከበደል ነፃ የሚያደርጉ፣+ጻድቁንም ፍትሕ የሚነፍጉ ወዮላቸው!+ ሕዝቅኤል 22:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ።+ ወለድና ትርፍ ለማግኘት* ታበድሪያለሽ፤+ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ።+ አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+ ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+ አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ* አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።+
12 በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ።+ ወለድና ትርፍ ለማግኘት* ታበድሪያለሽ፤+ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ።+ አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።